በጉራጌ ዞን የሚገኙ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የእናት ሀገራቸው ጥሪ ተቀብለው ወደ ሀገር ቤት ለሚገቡ ዳያስፖራዎች አቀባበል ለማድረግ መዘጋጀታቸው ገልጸዋል።
የጉራጌ ዞንና ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊነት አቶ ተመስገን ገብረመድህን ባስተላለፉት መልዕክት በዞኑ ደረጃቸው የጠበቁ አለም አቀፍ እውቅና ያላቸው ሆቴሎች፣ ሰውሰራሽና የተፈጥ የቱሪስት መስህቦች ለምሳሌ በዩኔስኮ የተመዘገበው የጥያ ትክል ድንጋይ መካነ ቅርስ፣ የጊቤ ሸለቆ ብሄራዊ የፓርክ፣ የምሁር እየሱስን ገዳም የኤነር አማኑኤል ገዳም፣ የምድረ ከብድ አቦ ገዳም፣የአብሬት መስጊድ፣ የቃጥባሬ መስኪድ፣ የዘቢሞላ ሀድራ፣ የዋቤ መዝናኛና የዘቢዳር ሰንሰላታማ ተራሮች እንዲሁም ዋሻዎችና ፏፏቴዎች በመኖራቸው ዳያስፖራው እየጎበኘ የሀገሪቱና የዞኑ አሁናዊ መረጃ ለአለም ማስተዋወቅ አለባቸው ብለዋል።
ወደ ጉራጌ ዞን የሚመጡ ዳያስፖራዎች በዞኑ ውስጥ ያሉ የቱሪስት መስህቦችና ቅርሶች እየጎበኙ ያሉን መልካም እድሎች ለመጠቀም መዋዕለ ነዋያቸውን በማፍሰስ ከራሳቸው አልፎ ህብረተሰቡ በስራ እድል ተጠቃሚ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
በመሆኑም የእናት ሀገር ጥሪ ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ ጉራጌ ዞን የሚመጡ እንግዶች ያሉን የቱሪስት መስህቦች፣ቅርሶችና መዝናኛ ቦታዎች ሰላማቸው ተጠብቆ ተቀሳቅሰው እንዲጎበኙና ቆይታቸው ያማረ እንዲሆን ዝግጅት መጠናቀቁም አስረድተዋል።
አቶ ኃይለማርያም ወልደሚካኤል በወልቂጤ ከተማ የኢንቲሳር ሆቴል ስራአስኪያጅ ከሆኑ ምክትል ኢንስፔክተር ሙሉነህ ለማ በወልቂጤ ከተማ የጆካ ኢንተርናሽናል ሆቴል የሰው ሀብት አስተዳደር ኃላፊነት ናቸው።
እንደኃላፊዎቹ ገለጻ የመንግስትን ጥሪ ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ዳያስፖራዎች ቀልጣፋና ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
የረድኤት ሆቴል ተወካይ አቶ መርሻ ወልደሰንበት የካፍ ሆቴል ስራ አስኪያጅ አቶ ወርቅነህ ታደሰ በበኩላቸው ሆቴሎቹ ደረጃቸውን የጠበቁ አገልግሎቶች ለዳያስፖራዎች ለመስጠት ቅድመዝግጅት አጠናቀው እንግዶቻቸውን እንደ አካባቢው ባህል አቀባበል ለማድረግ እየተጠባበቁ ይገኛሉ።
የዳያስፖራዎቹ ወደ አገርቤት መምጣት ሀገሪቱ ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ለውጪ አለም ለማሳወቅና አሸባሪው የትህነግ ቡድን በፈጸመው አረመኔያዊ ተግባር የወደሙ አካባቢዎች ለመጎብኘት እና ለተጎጂዎች አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ያግዛል ብለዋል።
በመሆኑም ሀገራዊ ጥሪን ተቀብለው ወደ ጉራጌ ዞን ለሚመጡ ዳያስፖራዎች ቆይታቸውም እንዲያረዝሙ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅታቸውን አጠናቀው የዳያስፖራዎች መምጣት በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል ።
ጉራጌ ዞን ምቹ የአየር ንብረት፣ አምራች የሰው ኃይል እንዲሁም አንጻራዊ ሰላም መኖሩ ለኢንቨስትመንት ምቹ በመሆኑ ዳያስፖራው መዋዕለነዋዩን ቢያፈስ ይበልጥ ተጠቃሚ እንደሚሆን ያነጋገርናቸው የሆቴል ስራስኪያጆች አስረድተዋል ።
በመጨረሻም የእናት ሀገር ጥሪ ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ እና ወደ ዞኒ የሚመጡ እንግዶች የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት መልካም ምኞታቸው ገልጸዋል።
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx