ሀገራዊ ለውጡን እናጸናለን፣ ለሰላማችን ዘብ እንቆማለን በሚል መሪ ሀሳብ ለውጡንና ታላቁ የህዳሴ ግድብ መነሻ ያደረገ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ በድምቀት ተካሂዷል።

ሀገራዊ ለውጡን እናጸናለን፣ ለሰላማችን ዘብ እንቆማለን በሚል መሪ ሀሳብ ለውጡንና ታላቁ የህዳሴ ግድብ መነሻ ያደረገ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ በድምቀት ተካሂዷል።

ለውጡ ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ በአንድነት በመሰባሰብ፤ በመደመር መንገድ የሀገራችን ከፍታ የምናረጋግጥበት የእይታ አድማስ የከፈተ እንዲሁም ኢትዮጵያዊነትና የብሔር ማንነት ሚዛናቸውን ጠብቀው እንዲጓዙ ያስቻለም እንደሆነ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ገልጸዋል።

ለውጡ ከሴራ ፖለቲካ ወደ መርህ ፖለቲካ፤ ከስርዓት አልበኝነትና ከቀውስ ወደ ሰላምና መረጋጋት፤ ከመገፋፋትና ከጥላቻ ወደ እርቅና አብሮነት እንድንሸጋገር ማድረጉን ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል፡፡

ይህንን እሳቤ ስር እንዲሰድና ባህል ሆኖ ለትውልድ እንዲሸጋገር የተጀመረውን ለውጥ ማስቀጠል ከሁላችንም የሚጠበቅ መሆኑን ተመላክቷል ፡፡

በዞናችን በቀጣይም ወንድማማችነት እና እህትማማችነትን በማጠናከር ከመፈራረጅ በራቀ አሰባሳቢ የሆነ ትርክት ለመገንባት ትኩረት ሰጥተን የምንሰራው ይሆናል ሲሉ አቶ ላጫ ጋሩማ አስገንዝበዋል፡፡

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ እንዳለ ስጦታ በድጋፍ ሰልፉ ላይ እንደገለጹት የከተማው ህዝብ ሰላም ፈላጊ፣ ታታሪና ስራ ወዳድ የሆነ በሀገሪቱ የመጣውን ለውጥ እንዲጸና ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።

መጋቢት24/2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ ህዝብ ሁለንተናዊ ልማት ለማረጋገጥና ለውጡን ለማጽናት የመሰረት ድጋይ ያስቀመጠበት ዕለት መሆኑን አቶ እንዳለ ገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *