ሀገራችን የተከፈተባት የሚዲያ ዘመቻና ጥቃት በመመከት ህዝቡ ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እንዲያገኝ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ተቋማት ከመቼውም ጊዜ በላይ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባቸው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ገለፀ።

በመረጃ የበለጸገና ምክኒያታዊ ማህበረሰብ በመገንባት የብልፀግና ጉዞው ለማጠናከር በሚደረጉ ጥረቶች ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ መምሪያው ጠይቀዋል።

መምሪያው ተቋማዊ የ2013 አመተ ምህረት አፈፃፀም ግምገማና በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ ላይ የሴክተሩ ተልእኮ ላይ የምክክር መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በወልቂጤ ከተማ አካሄዷል።

መድረኩ የመሩት የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቴ ወልደማሪያም እንዳሉት በመረጃ የበለፀገና ምክኒያታዊ ማህበረሰብ ለመገንባትና ሀገር አሁን ከገጠማት ፈተና ለመታደግ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ተቋማት ሀላፊነታቸው በተገቢ ሊወጡ ይገባል።

ለዚህም ሴክተሩ ከሁሉም ባለድርሻና ከሚዲያ ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሰራር አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባዋል ብለዋል።

ሚዲያ አሁን በደረስንበት ወቅት ትልቅ ጉልበትና መደራደሪያ መሳሪያ በመሆኑ ለዘርፍ ተገቢ ትኩረት መስጠትና ሁሉንም የሚዲያና ተግባቦት አማራጮች መጠቀም ይገባል ሲሉም ገልፀዋል።

አቶ መብራቴ አክለውም የዞኑ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ በመሆኑ የማህበረሰቡ የመረጃ ፍላጎት በዚሁ ልክ እያደገ ሲሆን በየደረጃው ያለው አመራርና ባለሙያ ያለው የሰው ሀይልና ግብአት አቀናጅቶ በመምራትና አመረጃጀት በማጠናከር ተገቢና ወቅታዊ መረጃ ለህብረተሰቡ ማድረስ አለበት ሲሉም ገልፀዋል።

ባለፈው አመት የሴክተሩ የሰው ሀይል አደረጃጀትና የግብአት ችግሮች ለሟሟላት በተደረጉ ጥረቶች ጅምር ዉጤቶች ማምጣት ተችለዋል ያሉት ሀላፊው ሆኖም ተቋሙ የዞኑ አጠቃላይ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ መሸከምና እንዲሁም የህዝቡ የመረጃ ፍላጎት ሟሟላት በሚችልበት ደረጃ ያልተደራጀ፣መሰረታዊ የሰው ሀይልና የግብአት ማነቆ ያለበት በመሆኑ ሁሉም ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።

የሴክተራችን አመራርና ባለሙያ አሁን ያለንበት ሀገራዊ ሁኔታው በመገንዘብ ህብረተሰቡ አካባቢዉ ሰላም በመጠበቅ፣ ጸጉረ ልዉጦች በመከታተልና፣አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥመው አሳልፎ ለህግና ለኮማኖድ ፖስቱ መረጃ በመስጠትና ለገራዊና ዞን አቀፍ ጥሪዎች ፈጣን ምላሽ እንዲሰጥ በማንቃት ሀላፊነቱ እንዲወጣም ጠይቀዋል።

በመድረኩ የተገኙት የጉራጌ ዞን ምክርቤት የሴቶች፣ወጣቶችና ማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ አህመድ ሀሰን እንዳሉት ህዝቡ የሚያነሳቸዉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙና ችግሮች እንዲፈቱ እንዱሁም ህዝቡ ጠያቂ ብቻ ሳይሆን አጋዥና ፈፃሚ እንዲሆን የኮሚኒኬሽን ተቋምና ባለሙያዎች ሚና የጎላ እንደሆነም አብራርተዋል።

በመሆኑም ተቋሙ አሁን የጀመራቸው ጥሩ ጅምሮች በማጠናክር ህዝቡ ተገቢ መረጃ እንዲያገኝና ለሀገራዊ ሰላምና መግባባቱ ማጠናከር አለበት ብለው ለዚህም በየደረጃ ያለው አመራርና የሚመለከታቸው አካላት ተቋሙ በማደራጀት ረገድ ሀላፊነታቸው መወጣት አለባቸው ሲሉም ጠቁመዋል።

የወልቂጤ ኤፍ ኤም ሬድዮ ኃላፊ አቶ ንጋቱ ወልዴ ከተሳታፊዎች የተነሳላቸዉ ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት እንዳሉት የወልቂጤ ኤፍ ኤም ሬድዮ ስርጭቱን በሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ የማስፋፋት ስራ የተሰራ እንደሆንም ገልፀው ቀጣይ አስፈላጊ ሁኔታዎች በሟሟላት ወደ ስራ ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ የተገኙ ተሳታፊዎችና ባለድርሻ አካላቶች በሰጡት አስተያየት ተቋሙ ለማጠነከርና ውጤታማ ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች አበረታች መሆናቸው ጠቁመው
የሚፈለገዉን ዉጤት እንዲመጣ የግብአት፣ የሰዉ ኃይል እና መሰል ማነቆዎች እንዲፈቱ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል ።

በየደረጃው ያሉ ጉለቶችን በመቅረፍና ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል በሴክተሩ የተያዘዉን ግብ ስኬታማ ለማድረግ እንደሚሰሩም ገልፀዋል።

በመጨረሻም ከወረዳዎችና ከተማ መስተዳደሮች በ2013 አመተ ምህረት የተሻለ አፈጻጸም ለነበራቸው የእዉቅና የሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።


በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:om https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *