በዞኑ በ2014 ዓመተ ምህረት ክረምት ወራት በተሰራ የበጎ አድራጎት ስራ ከመንግስትና ከህብረተሰቡ ይወጣ የነበረው ከ102 ሚሊየን ብር በላይ ማዳን መቻሉን የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ገልጿል።
በዛሬው እለት በበጋ የበጎ አድራጎት ስራ የተሰማሩ ወጣቶች እና የህብረተሰብ ክፍሎች በቡታጀራ ከተማ የሻባብ የወጣቶች መዝናኛ ማእከል የማጽዳትና የችግኝ ኩትካቶ ፕሮግራም አካሂዷል ።
የጉራጌ ዞን ምክትል የመንግስት ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገብረመስቀል በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው እንዳሉት ሀገሪቱ ከገጠማት ፈተናዎች ለመውጣት በጎ አድራጊ ወጣቶች እየሰሩት ያለው የበጎ ፈቃድ ተግባራት አጠናክረው ማስቀጠል እንደሚገባቸው ተናግረዋል።
ለአብነትም በአካባቢው ጥበቃ፣ለመከላከያ ሰራዊት ደም ልገሳ በማድረግ፣የዘማች ቤተሰብ በመደገፍና በልማታዊ ስራዎች ተሳታፊ እየሆኑ እንደነበር አመላክተዋል።
አቶ አለማየሁ አክለውም በዞኑ በምስራቅ መስቃንና በማረቆ ወረዳዎች ተፈናቅለው አሁን ግን ወደ ቄያቸው ለተመለሱ የህብረተሰብ ክፍሎች በጉልበት፣በቁሳቁና በሀብት አሰባሰቡ ላይ ወጣቱ እያደረገ ያለው ተሳትፎ አጠናክሮ ማስቀጥል ይገባል ነው ያሉት።
ከፊት ለፊታችን ሰፊ የበልግ ስራዎች የምንሰራበት ወቅት በመሆኑ ወጣቶችም አቅም ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ጓሮአቸው በማረስ እና የተለያዩ የበጎ ስራዎቻቸው አጠናክረው እንዲያስቀጥሉ አቶ አለማየሁ መልእክታቸው አስተላልፏል።
የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ምክትል እና የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዶ ድንቁ በበኩላቸው በበጋው የበጎ አድራጎት ስራ ከ1መቶ 82ሺ በላይ ወጣቶች በማሳተፍ ከ4መቶ 11ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል።
በበጋው የበጎ አድራጎት ስራ በ13 ዘርፎች የሚሰራ ሲሆን እንደ ወቅቱ ሁኔታ ደግሞ የትምህርት ቤት ወንበሮችን በማስጠገንና አጥሮች በማጠር ፣ችግኞች የመንከባከብ እንዲሁም የጽዳት ስራዎች እና ሌሎችም እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል አቶ አብዶ ድንቁ።
በዚህም እስካሁን በበጋ በጎ አድራጎት ስራ በመንግስትና በህብረተሰቡ ይወጣ ከነበረው 102 ሚሊየን ብር በላይ ማዳን መቻሉ አስታውቀዋል።
በስነ ምግባር የታነጸ እና ከሱስ የጸዳ ትውልድ ለማፍራት የወጣትቶች ሰብዕና ላይ በትኩረት መሰራት አለበት።ለዘርፉም የሚመለከተው ሁሉ የድርሻውን እንዲወጣ አቶ አብዶ ድንቁ አሳስበዋል።
የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ጽ/ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ሽፉ መሀመድ እንደገለጹት በበጎ አድራጎት ስራው በከተማው የሚገኙ ለ16 አረጋዊያን ቤት የማደስ እና በሌሎች ተግባራት እርዳታ ሲደረግ ቆይቷል ብለዋል።
በቀጣይም በክረምት ወቅት ያልተሰሩ ተግባራቶችን በመለየት በበጋው ወቅት በትኩረት ይሰራበታል ነው ያሉት።
ወጣት ቋሲም ግርማ ፣ወጣት ጀማል ዶርሞሎ እና ሙንተሀ ሹሁር የበጎ አድራጎት ስራ ተሳታፊዎች ሲሆኑ የበጎ አድራጎት ስራዎችን ሲያከናውኑ ከፍተኛ የሆነ የአእምሮ እርካታ እናገኛለን ብለዋል።
ይህን መነሻ በማድረግ አካባቢያቸው በመጠበቅ፣ለተቸገሩ ወገኖችን በገንዘብ፣በቁሳቁስ፣በጉልበትና በሌሎችም እርዳታ እናደርጋለን ያሉ ሲሆን ለቀጣይም በሀገራዊ ጉዳዮች፣የተቸገሩ በመርዳት፣በጽዳት፣በልማታዊ ስራዎች ከመንግሥት ጋር በመቀናጀት የተሻለ ስራ እንሰራለን ብለዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx